ጎበና ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሕይወት (1810-1881) - ለዘመናዊት ኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ታላቅ ሚና ስለተጫወቱት የፖለቲካ ሰውና የጦር መሪ የራስ ጎበና ዳጪን የሕይወት ታሪክ የያዘ መጽሐፍ ነው።
በአራት ክፍሎችና በዓሥራ አራት ምዕራፎች ተዋቅሮ ክፍል አንድ ከዋናው የታሪክ ዳሰሳና ትንተና በፊት ታሪካዊውን ዳራ ለመተረክ ይሞክራል። ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ጎበና ሊደርስ ከቻለበት የወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ የእውቅና ጣርያ ድረስ ያለፈባቸውን በፈተና የተሞሉ፣ የዚያኑ ያክል በውጤት የታጀቡ የሕይወት ልምዶቹን ለመዳሰስ ጥረት የሚያደርግ ሲሆን፤ ሦስተኛው ከዚሁ ተያያዥ በሆነ መልኩ ጎበና የተጎናጸፈውን እውቅና እንደምን አድርጎ ሀገራዊ ፋይዳ ወደአለው ነገር እንደለወጠ ለማሳየት ይጥራል። ክፍል አራት የጎበና የመጨረሻ ዘመናት ያለ አቻ ወራሽ ሲጠናቀቁ የኦሮሞ ሕዝብ የተጋረጠበትን ከሀገርና ከመንግሥት ባለ&